የGoogle Chrome እና የChromeOS ተጨማሪ የአገልግሎት ውል

ለመጨረሻ ጊዜ የተቀየረው፦ 23 ጃንዋሪ፣ 2025

Chrome ወይም ChromeOSን በመጠቀምዎ https://policies.google.com/terms ላይ በሚገኘው የGoogle አገልግሎት ውል እና በእነዚህ የGoogle Chrome እና ChromeOS ተጨማሪ አገልግሎት ውል ይስማማሉ።

እነዚህ የGoogle Chrome እና የChromeOS ተጨማሪ አገልግሎት ውል በተፈጻሚው የChrome እና Chrome OW ኮድ ስሪት ላይ ይተገበራሉ። አብዛኛው የChrome ምንጭ ኮድ በክፍት ምንጭ ፈቃድ ስምምነቶች chrome://credits ላይ ባሉ የክፍት ምንጭ ሶፍትዌር ፈቃድ ስምምነቶች መሠረት ከክፍያ ነጻ የሚገኝ ነው።

የእርስዎ የተወሰኑ የChrome እና ChromeOS ክፍሎችን መጠቀም ለሚከተሉት ደንቦች ተገዢ ነው፦

AVC

ይህ ምርት በAVC ፓተንት ፖርትፎሊዩ ፈቃድ መሠረት ሸማች የሚከተሉትን ለሚያደርጉባቸው የግል አጠቃቀም ወይም ክፍያ የማያገኙባቸው ሌሎች አጠቃቀሞች ፈቃድ የተሰጠበት ነው፦ (i) በAVC መስፈርት («የAVC ቪዲዮ») መሠረት ቪዲዮን በኮድ ማስቀመጥ እና/ወይም (ii) በግል እንቅስቃሴ ላይ ሲሳተፉ በነበረ ሸማች በኮድ የተቀመጠ የቪዲዮ ኮድ መፍታት እና/ወይም የAVC ቪዲዮን ለማቅረብ ፈቃድ ከተሰጠው የቪዲዮ አቅራቢ የተገኘ የቪዲዮን ኮድ መፍታት። ለሌላ ማንኛውም አጠቃቀም ምንም ፈቃድ አይሰጥም ወይም በውስጥ ታዋቂነት እንደተሰጠ አይቆጠርም። ተጨማሪ መረጃ ከMPEG LA, L.L.C. ሊገኝ ይችላል። HTTP://WWW.MPEGLA.COM ይመልከቱ